Tuesday, July 31, 2012

ሰበር ዜና ! የጅዳ ቆንስል ግቢ የውሃ ገንዳ ሰው በላ !

   ኢትዮጵያዊቷ ሞታ ተገኘች !

 ይህች ኢትዮጵያዊ ሞታ የተገኘች ው በጅዳ ቆንስል ኢንባሲ ግቢ ውስጥ በገኘው የውሃ ገንዳ ውስጥ ሲሆን ወቅቱም  በግምት 3፡15 ሌሊት አካባቢ መሆኑን ለማዎቅ ችያለሁ፡፡ የዚህች እህት ሞታ መገኘት እንደሰሙ ምክትል ቆንስል ሸሪፍ በቦታው በመገኘት የአደጋ ጊዜ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ሬሳውን ከጉድጓድ አውጥተው ነብሷ ከስጋዋ ያልተለየውን  እህት ለማዳን ሲታገሉ የአይን ምስክር ነበሩ፡፡ ሆኖም ሙከራቸው ሁሉ ያልተሳካላቸው የቀይ ጨረቃ ሃኪሞች የተቻለ እርዳታ ለማድረግ ወደ ሆስፒታል በአፋጣኝ እንደወሰዷትና አምባሳደር መርዋን በድሪም ሬሳው ወደ አንቡላን ሲገባ መደረሳቸውን ለመረዳት ችያለሁ፡፡
 በጅዳ ቆንስል ኢንባሲ ግቢ ውስጥ በገኘው የውሃ ገንዳ
   በቦታው ለመገኘት እንደታዘብኩት በወቅቱ የነበሩት መርማሪዎች እጅና እግሯ ታስሮ እያለ በገንዳው ውስጥ ገብታ ስለሞተችው ስለዚህችው ልጅ አሟሟት ዙሪያ ግራ በመጋባት መስቀለኛ ጥያቄዎችን ሲጠይቁ በቦታው ነበርኩ፡፡ የወቅቱ የቆንስሉ ዘበኛ የነበሩት አቶ ገሬ ስለ ተፈጠረው ሁኔታ ማብራሪያ ሲሰጡም ሟች ገና ከምሽቱ በግምት 4፡00 ሰአት አካባቢ  ወደ ካፍቴሪያው ግቢ እንደመጣችና የዓዕምሮ ህመምተኛ በመሆኗ ከመጮህ በቀር አድራሻና ስሟን ባለመናገሯ እጅና እግሯን በማሰር ወደ ጊዜያዊ መጠለያው እንዳስቀመጣት ተናግሯል፡፡ ከዚያም አቶ ገሬ ሲያስረዳ ከምሽቱ 2፡00 አካባቢ ግቢን በሙሉና ገንዳውን ጨምሮ ከሰወች ጋር በመሆን ቢያፈላልጋትም የውሃው ገንዳ ገበድ ያለ ብረት መዝጊያ ገርገብ ብሎ እንዳገኘው በመብራት ቢመለከትም ምንም ነገር እንዳላየ ገልጿል፡፡ አቶ ገሬ በማከል ሲናገር ብዙም ሳይቆይ ግን ልጅቷ ከገንዳው ገብታለች ብሎ በመጠራጠሩ ገንዳውን ለማስፈተሽ ለፖሊስ ጥሪ ማድረጉን ተናግሯል፡፡ ከዚያ ፖሊስ መጥቶ ገንዳው ሲፈተሽ የዚህች ሬሳ ተገኝቶ በፖሊሶች እንደወጣ በቦታው ተገኝቸ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ በመጨረሻም የቆንስሉ ዘበኛ ለጥያቄ ወደ ጣቢያ መወሰዳቸውን ተመልክቻለሁ፡፡ እኔን ጨምሮ ዲፕሎማቶችና የኮሚኒቲ ሃላፊዎች ንጋት ላይ ወደ የቤታችን ተመልሰናል፡፡
   ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካቶች ያበዱ የኮንትራት ሰራተኞች በቆንስሉ ግቢና በጊዜያዊው መጠለያ ከአርባ የማያንሱ በአሁኑ ሰአት እንደሚገኙ ከቆንስሉ ያገኘሁት መረጃ ያስረዳል፡፡ በቆስል ከዚህ በፊት ተጠልለው የነበሩ አንዳን እህቶች በቆንስሉ በተጠጋንበት ቆንስል መስሪያ ቤት ዘበኛ አቶ ገሬ በሴትነታቸው ሊያጠቋቸው እስከመደብደብ እንደደረሱ ለቆንስል መስሪያ ቤቱ መከሳቸውን በመረጃ ማቅረቤ አይዘነጋም ፡፡ ዛሬ በዚሁ ጉዳይ ያነጋገርኳቸው አምባሳደር መርዋን ከዚህ በፊት ስለተፈጸመው ጥፋት ጠይቄያቸው አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደ ገልጸውልኛል፡፡  
   

No comments:

Post a Comment