Friday, July 27, 2012

የማለዳ ወግ . . ..የጅዳ ሙስሊማን ጉዳይ ! "ማን ይናገር የነበረ ፤ ማን ያርዳ የቀበረ !" እማኝ ፤ ምስክር እያለ ብዥታ ሊኖር አይገባም !

   ከዚህ በፊት ባስነበብኳችሁ የማለዳ ወግ "አክራሪ" ተብየውን አህመዲን ጀበልን ፤ ጓዶቹንና የመጅልስ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ሳውቃቸው ! በሚል ያዘጋጀሁትን ዳሰሳ ወቅታዊ ወግ ላሰካካ ካለብኝ የግል የስራ ጫና በተጓዳኝ እዚህ እዚያ ስል ነው የሰነበትኩት፡፡ በተለይም ከአስራ አምስት አመታት በላይ በኖርኩበት አካባቢ የታዘብኩት ግልጽ እውነታ ቢኖር ሙስሊሙ ማህበረሰብ በመጅሊስ መሪዎች ላይ የሚያሰማው ሮሮ እያደር በመሪዎቹ ላይ እምነት ማጣቱና ጥላቻው ከፍ ማለቱን ነው፡፡ 

ከወራት በፊት ጥያቄውን ያቀረቡ አባቶች በከፊል
ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ሲመክሩ
እናም ከራሴ ጋር መክሬ ስለመጅልስ ሃላፊዎችና በጸሎተኛው ዙሪያ ሰለደረሱ እጅግ በጣም ብዙ በድሎች ለአመታት ከኦምራና ሃጃጅ ምዕምናን የተነገረኝንና የማውቀውን ፍንትው ያለ መረጃዎች ላለመጠቀም ወሰንኩ፡፡ አዲስ ከነዋሪው አዲ የሚነገረኝን መረጃ ብቻ ላቀርብ ከአሴ ጋር ቃል ገብቸ ተንቀሳቀስኩ፡፡ እናም ዘወር ዘወር ብየ ነዋሪው ልጠይቅ ወስኛልሁ መጅልሱን የሚያመሰግን አጋጥሞኝ ባያውቅም በጎ ጎን ካለው ለመጠየቅ አለያም የአዎልያን የመጅልሱ ይውረ መፈከር ከድ አድርገው ድምጻቸውን የሚያሰሙትን ድግሞ "ለምን መጅልሱ ይውረድ ትላላችሁ ?" ስል ልጠይቅ የተለያዩ ወገኖችን ለማነጋገር ያደረግኩት ሙከራ ጠንከር ያለ የእኔኑ የቀድሞ መረጃ የሚያጠናክር እንጅ የተለየ ሆኖ በማግኘቴ አልደነቀኝም ፡፡ በዚህ ሁኔታ ማስታዎሻየን ሞነጫጭሬ ሃሳቤን ላጋራችሁ ስንተፋተፍ ባሳለፍነው ሳምንት በጅዳ ስለተካሄደው የተቃውሞ ስብሰባ  ያልጠበቅኩት የተወለካከፈ መረጃ ሲነገር አጋጠመኝ፡፡ እናም መሪየን መልስ ወደ ሚያሻው አዞርኩት ! እማኝ ምስክር እያለ ብዥታ ሊኖር አይገባም ስል መረጃዎቸን ሰባስቤ ከዚህ ማስታወሻ ጋር ላደርስዎ ፈቀድኩ !  

   ለበርካታ ወራ በአዎሊያ እየተሰባሰቡ " መንግስት ከሃይማኖት ጣልቃ አይግባ!" የሚሉና " መጅልስ ይውረድ ! " በማለት ድምጻቸውን የሚያሰሙ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ " አግባብነት ያለው ነው!" ሲሉ በሳውዲ አረቢያ ሪያድና በጅዳ ኢትዮጵያን ሙሊሞች ለአዎሊያው እንቅስቃሴ ድጋፋቸው በመግለጽ መንግስት ጉዳዩን መርምሮ መፍትሄ እንዲያፈላልግ አቤቱታ የማቅረባቸውን ይታወሳል ፡፡  በተለይም ከሳምንት በፊት በአዎሊያና በአንዋር መስጊድ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ቁጥራቸው በርካታ ነዋሪዎች "መንግስት ጉዳዩን በአጽኖት ይመረምረውና መፍትሄ ሊሰጥበት ይገባል እንጂ መብታችን እናከበር ያሉ ዜጎችን በሃይል ለማንበርከክ መሞከር ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ! " የሚል አንድምታ ያለው ውይይት በማድረግ የአቋም መግለጫ መልዕክታችውን ሃምሌ 8 ቀን 2004 አ.ም ሲያቀርቡ የአይን እማኝ ነበርኩ፡፡ 


    ነዋሪዎች የመጀመሪያውን ጥያቄ ከወራት
    በፊት ለውጭ ጉዳይ ባለስልጣኑ ሲያስረክቡ
በእለቱ በተለይም በጅዳ በተደረገው ስብሰባባ  ስሜት ተጠራርተውና ለስራ ጉዳይ ወደ ኮሚኒቲው ካፊቴሪያ ጎራ ባሉበት አጋጣሚ እንደተሰባሰቡ የገለጹልኝ ነዋሪዎች ባደረጉት ስብሰባ የመንግስት ሃላፊዎች ስብሰባውን በመካፈል የነዋሪውን ስሜት በማድመጥ ለመንግስት ያስተላልፉ ዘንድ ቢጋበዙም ስብሰባው በህገወጥ መንገድ ያለ ፍቃድ የተካሄደ በመሆኑ ለመሳተፍ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ነዋሪውን አስቆጥቶት ነበር፡፡ ምንም እንኳ የመንግስት ሃላፊዎች ስብሰብውን ባይካፈሉም ለሰአታት በተደረገ ሽምግልና የተሰብሳቢውን የአቋም መግለጫ ለቆንስል ሃላፊዎች እንዲረከቡ መደረጉን የኮሚኒቲው ም/ሊቀመንበር አቶ አህመድ አባ ጀበል ገልጸውልኝ ነበር ፡፡ በዚሁ ሽምግልናም ም/ሊቀ መንበሩን ጨምሮ የህዝብ ግንኙነትና የማህበራዊ አገልግሎት አስታራቂ ኮሚቴ ሃላፊዎች ባደረጉት ጥረት ፍጥጫውን በማርገብ መቻሉን በገለጹልም መሰረት ሙሉ ዘገባው እጥርና ምጥን ለማድረድ ተሞክሮ በጀርመን ራዲዮ ዜና መጽሄት ቀዳሚ ዜና በትንታኔ ሆኖ ቀረበ !


  በተቃውሞው በስብሰባ መጨረሻ ጉዳዩን ለመከታተል የሚችሉ ኮሚቴ ሲያዋቅሩ አሁንም በቦታም በመገኘት አስፈላጊ መረጃዎችን አግኝቻለሁ፡፡ ከዚያ ወዲህም ኮሚቴው እየሰራ ስላለው ስራና ስለ አጠቃላይ ግንዛቤን አገኝ ዘንድ የኮሚቴውን እንቅስቃሴው ለመረዳት ያደረግኩት ተደጋጋሚ ሙከራና ጥረት ግን አልተሳካም፡፡ ስለኮሚቴው በቅርበት ከሚያውቁት ለማጣራት ባደርግኩት ሙከራም የገመትኩት ተስፋ አስቆራጭ ዜና ደረሰኝ ፡፡ "ህገ-ወጥ" በተባለው ስብሰባ የተመረጡት የኮሚቴ አባላት በቆንስሉ እውቅና እንዳልተሰጣቸውና በዚህም ምክንያት ኮሚቴው "አለ" ከማለት "የለም" ማለቱ እንደሚቀል አሰተያየታቸውን የሰጡኝ ነዋሪዎች ፍርሃት ስጋቱን አጫውተውኛል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለም ከላይ በጠቀስኩት የመጅልስ መሪዎች ጉዳይ መረጃና አስተያየት ለማዳመጥ ሳነፈንፍና ከአንዳን ነዋሪዎች ጋር ባደረግኩይ ግልጽ ውይይት እንደ ተረዳሁትም በዚህ ስብሰባ መወያያ የተመከረባቸው አበይት ነጥቦች ሌላ መልክ ተሰጥቷቸው ሲነገሩ አጋጥሞኛል፡፡ ከዚህም አልፎ ስብሰባውን ባልተካፈሉ ነዋሪዎች መካከል የተዛቡ መረጃዎችን ሲተላለፉ በመስማቴ ደስታ አልተሰማኝም፡፡ አባቶች "ማን ይናገር የነበረ ፤ ማን ያርዳ የቀበረ !" 

 ከወራት በፊት የሃይማኖት አባቶች
                       መረጃዎችን ሲያሳዩ . . .
እንደሚሉት በቦታው ነበርኩና የእማኝነት መረጃየን ማቅረብ ተሰማኝ፡፡ በዚሁ ዙሪያ ያሰባሰብኳቸውን የተንቀሳቃሽ ምስልና የድምጽ ማስረጃዎች ግልጽ አደርግ ዘንድ ሃላፊነት ተሰማኝ ! የተፈጠረውን የመረጃ መፋለስ ብዥታ ለመቅረፍ ይቻላል ዘንድም የስብሰባውን ግልጽ ሂደት ያሳያሉ ያልኳቸውን አንኳር አንኳር ሃሳቦችን ለማቅረብ ዝግጅቴን ጨርሻለሁ፡፡ ያም ሆኖ የተንቀሳቃሽምስሎችን እርዝመት ከግምት ውስጥ በማስገባት ለማሳጠርና አላስፈላጊ ድግግሞች እንዳይፈጠሩ ሙከራ ማድረጌን ከተረዳችሁልኝ ደስ ይለኛል፡፡ በየረፈ መረጃውን በሶስት ክፍል ያዘጋጀሁት ሲሆን ከውይይቱ በኋላም በወቅቱ ከአንዳንድ ተሰብሳቢዎችና ከጅዳና አካባቢው ኮሚኒቲ ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር በስብሰባው ዙሪያ ያደረግኩትን ቃለ መጠይቅ በአራተኛ ክፍል የሚቀርበው ይሆናል፡፡ እማኝ ምስክር እያለ ብዥታ ሊኖር አይገባም የሚል እምነት አለኝና እነሆ የዝግጅቱን መግቢያ ይመልከቱ !

በዚህ ዙሪያ አስተያየትዎን የምቀበልዎ በደስታ ነው  !

ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ


No comments:

Post a Comment