 |
| ዶር እሌኒ |
ራት ልበላ ድንች ቀቀልኩ ! አልበስል ብሎ ቢያቸግረኝ ፊቴን ወደ ኮምፒውተሬ
አፍጥጨ በማለዳው ከወዳጀ ከወንድም ደስታው ወገኛውጋር የደመቀ ወግ ይዘናል፡፡ ኢን ቦክስ inbox በሚሉት የጓዳ በር ፡) ደሱ በወጋችን መሃል
አንድ ጽሁፍ እንዳነብ ጠቆመኝ ፡፡ ለካስ እኔን እያጫወተም ያነብ ኖሯል ! ደስታው ወደ ጠቆመኝ የዶር እሌኒ መጣጥፍ ሳመራ ፈጣኑ ወዳጀ
ከዶር እሌኔ መጣጥፍ ግርጌ"
ፓ! ይሄ ነው እንግልዘኛ፤ የገባኝን ያህል ተረድቼዋለሁ ያለምንም አስተርጓሚ:: ጻፈችው ሴትዮዋ! ጭርጭር አድርገው ከቦታዋ "ሲያሽቀነጥሯት" እኔ ኢትዮጵያዊነቴን እንጂ ዘሬን አላውቅም ብላ አረፈች. . .የኛ ሀገር እንግልዘኛና ህልም እንደፈቺው ነው እንግዲህ:: አንብቧት እና የራሳችሁን ፍቺ ውሰዱ እናንተ ደግሞ:: "Ethiopia is ours, to claim, to build and to restore. Rather than engage
in destructive ethnic bigotry, far better to embrace all of what we are and to
build together a better future for our children. " ዶር እለኒ ዘውዴ ገብረመድህን:: " የሚል አስተያየቱን ለጥፎበት
አገኘሁ ! የደሱን
" ፓ" አድናቆቱን አውቃታለሁና እኔም እንደሱ እያዋራሁት ወደ ጠቆመኝ እያባበለ ውስጥ የሚሰረስረውን መረጃ በጥድፈት
አነበብኩት ፡፡
. . . በሚነሽጠው ግሩምና ድንቅ በሆነው የዶር እሌኒ
መጣጥፍ ኢትዮጵያን ደግሜ ደጋግሜ አየኋት . . . እናቴን !. . . "የሰው ልጅ በቃላት መንፈስን
እውን ይፈጥራል!" ምናምን እያልኩ በስነ ጽሁፍን ሃያልነት፤ የፈጣሪን የአፈጣጠር ረቂቅ ጥበብ እስከ መመርመር ያደረሰኝን
ያህል አድናቆት ለአምላክ አቅርቤ ቃላት ላጣሁለት ማራኪ መጣጥፍ ከደሱ አስተያየት ለጥቄ ለጠፍኩ እንዲህ በማለት እኔም ለጠፍኩ . . .
እውነት እውነት እልሃለሁ ደሱ በተዋበውና በረቀቀው የክቡር እህት ዶር እለኒ ዘውዴ ገብረ መድህን መጣጥፍ የዥጉርጉሩን የትውልድ ሃረግ መሰረት ክቡሩን ኢትዮጵያዊነትን ለማየት ችያለሁ ! ". . . Ethiopia is ours, to claim, to build and to
restore. Rather than engage in destructive ethnic bigotry, far better to
embrace all of what we are and to build together a better future for our
children. . ." ዶር እሌኒ እውነት ብለዋል ! ኢትዮጽያ የኛ ናት በጋራና በመተሳሰብ የምንገነባት ! ሁሉም የመጣጥፉ ክፍሎች አስተማሪ ናቸው ! ለአድናቆት ቃላቶች ያጥሩኛል !"
ያ የሆነው
ትናንት ነበር ! ምሽት ላይ ድንች ቀቅየ አልበስል ሲለኝ ኮምፒውተሬ ከፍቸ አሁንም በተደጋጋሚ የፌስ ቡክ ጓደኞቻችን ዶር እሌኒን መጣጥፍ
እየተደመሙ የሚለጥፉትን እያስተዋልኩ እናንተኑ
ወደ ትናንቱ ትዝታየ መጎተቴ ያለ ነገር አይደለም፡፡ እንደ ትናንቱ ወደ ሰፋ ወግ ልወስዳችሁ ሳይሆን ምሽት ላይ ያጋጠመኝንና
የፈጣሪን ስራ ለማድነቅ ነው ! ድንች እንደቀቀልኩ አትርሱ ! ከመከረኛዋ ፎቴ ላይ ኩርምትም ድህረ
ገጾችን ስጎራጉርና ካፈጠጥኩበት ኮንፒውተር ያስነሳኝ ሆዴን የሸረሸረው ረሃብ ነበር ! ከሚገነፋፍል ከሚንተከተከው ብረት ድስት ውስጥ
እየተቀቀለ ያለውን ድንች በማንኪያ ገልበጥ ገልበትካደረግኩ በኋላ ማንኪያውን ወርወር አድርጌ ሹካ ጨበጥኩ፡፡ ቀጠልኩና የድንቹን
መብሰል አለመብሰል ለማረጋገጥ ወጋ ወጋ እያደረግኩት አቶ ድንች ግን አልበሰለም ! እየሞረሞረኝ ቢሆንም ረሃቡን ለመርሳት ወደ
ፌስ ቡክ ዞር ስል "ልብ ካላየ አይን አያይም" የሚሉት በኔ ደርሶ ከ15 በላይ መልዕክትና ከ48 በላይ የወዳጅነት
ጥያቄ ከኔው ገጽ ጫፍ ተደርድሮ ጠበቀኝ !
ከቀናት
በፊት እየሆነ ያለወ ሲያሳስበኝ በሙስሊማን ላይ
እየሆነ ያለው እጅግ በጣም ያሳዝናል ! ስል
የጻፍኩት ማስታወሻ ዋንኛ ምክንያቱ በሙስሊም ወገኖቸ ላይ እየሆነ ያለውን ዙሬ አዟዙሬ ሳየው አልዋጥልህ ስላለኝ ነበር፡፡ ይህ
ሆነና እውነቱ የልቤን አውጥቸ በማጋራቴ ብዙዎች ደስታቸውን በአካልና በስልክ እየደወሉ የገለጹልኝን ያህል በፌስ ቡክ ገጼ ላይ ለወዳጅነት
የሚጠይቁኝ ቁጥር ተበራክተዋል፡፡ እኔም ቢሆን የማምንበትን እምነት ለማራድ ነፍሴ ከፈቀደ ከራርሟልና ማንም ይሁን ማን ለወዳጅነት
ከፈቀደኝ በሬን ወለል አድርጌ ከከፈትኩት ቆይቻለሁ ፡፡ ያም ሆኖ በአንድ ቀን ውስጥ እንዲህ በጥቂት ሰአታት ልዩነት ጉድኝነት ጥያቄውና
መልዕክቱ እንዲህ ሆኖ አይቸው አላውቅምና "ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ " ስል ራሴን መልሸ መላልሸ መጠየቄ ባይቀርም
በጻፍኩትና በምጽፈው ዙሪያ ራሴን መጠየቁ አላስፈለገኝም፡፡ አስረግጨ የማውቀውንና ነፍሴ የፈቀደውን ስለማደርግ ራሴን ዞሮ ማጠየቁን
አልደፈርኩትም ፡፡ ብቻ ይህ አጋጣሚ በጉዳዩ ዙሪያ እየሆነ ያለውን እንድመረምር ጋበዘኝ. . . የሙስሊማን ሰላማዊ መብት
ጥያቄ ሲነሳና ሃሳቤን ስገልጽ ያገኘሁት ህብረት የሚታይበት ምላሽ ወደ አንድ መጣጥፍ
እንዳመራ አስገደደኝ ! "ድር ቢያድር "ብየ ጀመርኩትና እንደገና ሰረዝኩት . . . ደጋግሜ የተለያዩ ርዕሶችን አውጥቸ አወረድኩና
የመጨረሻዋን ተስማሚ ርዕስ በብዕሬ ቀለም በነጩ ወረቀት ላይ ከተብኩ"የዜጎችን ህብረት የሚሹት የሙስሊማኑና የኮንትራት ሰራተኞች
ህገ መንግስታዊ
የመብት ጥያቄዎች ሲዳሰሱ !" በሚል ርዕስ ዙሪያ የኮንትራት ሰራተኞችን አበሳና የመብት ይከበርልኝ ጥያቄ ከሙስሊማኑ ሰላማዊ
ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ ዚሩያ በቀጣይ ቀናት ለመዳሰስና ለመንሸርሸር ወሰንኩና ይህንንም በዚህ ዘግቸ ወደ ወቅቱ ምልከታየን
ቀጠልኩ፡፡ . . .
. . .
ይሄ የኔ ድንች በቀላሉ እንደማይበስል ስለተረዳሁ "ትንሽ ሳት ይምታው ይብሰል!"
በማለት ተውኩት፡፡ ድንቸ ሙክክ ብሎ እስኪበስል
መልዕክቶችን ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ባንድ ወቅት የጅዳ ቆንስል ከፍተኛ ሃላፊ ከነበሩ ወዳጀ ጀምሮ የማላውቃቸው በርካታ ወገኖቸን መልዕክት
በደስታ ነበር የቃኘሁት፡፡ የቆንስሉ ሃላፊ ያልኳችሁ ሰው መልዕክት ሰላምታ ብቻ እንጂ እንደቀሩት ወገኖቸ መልዕክት ወደ ምስጋና
ሆነ ወደ ሌላ ጉዳይ አልዘለቁም፡፡ የቀሩት የዛሬ ምሽት መልዕክቶች ግን ተመሳሳይ የአድናቆትና የምስጋና ብቻ ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡
የሚገርመው ነገር ቢኖር ከተደረደሩት ሁሉ መልዕክቶች አንድም የሚያስከፋ መልዕክት አለመኖሩ ነው፡፡ ፍጹም ስሜትን የሚነኩ ምስጋናዎች
ነበሩ ! ለተጻፈልኝ አስተያየትና ምስጋና ሁሉ ተገቢውን ምላሽ ሰጥቸ ብዙሃን ባደነቁት ባወደሱት ወገኖቸ ቀዳሚ ነገር ዙሪያ ለጀመርኩትን
መጣጥፍ ግብአት የነዋሪውን አስተያየት ለመሰብሰብ መንቀሳቀስ የጀመርኩ ከመሸ ነበር፡፡ "አክራሪ"
ተብየውን አህመዲን
ጀበልን ፤
ጓዶቹንና የመጅልስ
ከፍተኛ ባለስልጣናትን
ሳውቃቸው ! በሚል ለጀመርኩት መጣጥፍ በከተማው
መናኘቱን የተረዳሁት መረጃ ለመሰባሰብ በከተማው ሽሻ ቤቶችና በኮሚኒቲው አዳራሽ ጎራ ባልኩባቸው አጋጣሚዎች ያገኘኋቸው ወዳጆቸ ሞቅ
አድርገው ከመጨበጥ ባለፈ እያቀፉ ሲስሙኝ አልነበረም፡፡ በቀጥታ የሳውዲ
ኢትዮጵያውያን ብሶትና ሃሳብ ይገልጻል ባሉት" የመጅልስ ይውረድ!" ጥያቄ ዙርያ ብዙ አወጋን፡፡ በመጅሊስ ሃላፊዎች
አይዎክሉንም የሚለውን ለማጠናከር በነዋሪው የሚነገሩና የሚሰነዘሩ አስተያየቶች እኔ ከምለው ጠንከር ያሎ ሆነው አገኘኋቸው፡፡ እንዲህ እንዲያ ስል አምሻሽቸ ወደ ቤቴ ተመለስኩ. . .
አሁን ለአንድ
ሰአት ያህል የተጣደው ድንቸ እንደበሰለ እርግጠኛ ነኝ ፡፡ ፈንጠር ብየ ከፎቴው ተነሳሁና ወደ ጓዳ አመራሁ ! ሹካውን ይዥ የሚንፈቀፈቀውን
የፈላ ውሃ አልፌ ድንቹን ወጋ ወጋ ሳደርግ ሞከክ ብሎ በስሏል፡፡ የድስቱን ሁለት ጀሮዎች በጨርቅ አፈፍ አደርጌ ወደ
ቧንቧው በመውሰድ የፈላውን ሙቅ ውሃ በማፍሰስ የቧንቧ ውሃ ቸለስኩበት ! እንፋሎቱ ተጉለል ሲል ደጋግሜ በቸለስኩት ውሃ ድንቸን
አባርደኩ፡፡ እርቦኝ ልበላ ስንገበገብ ከተቀቀለው ድንች መካከል አስገራሚ የልብ ቅርጽ ያለት አንዲት ድንች አይኔን ሳበችው ፡)
እንደ መሳቅ እንደ መገረም እያልኩ ካፈጠጥኩበት ኮንፒውተር ዳር ድንቸን አስቀምጨ የፈጣሪ ስራ ለማድነቅ ፎቶ ማንሳት ያዝኩ ! በአጋጣሚዎች
ሁሉ ተደመምኩ ጠዋት በዶር እሌኒ አእምሮን የመጨምደድና የመግዛት ሃይል ባላቸው ህይዎትን የሚሰጡ ማራኪ ቃላቶች ፤ ምሺት ላይ በአስገራሚዋ
የልብ ቅርጽ ያላት የኔ ድንች የፈጣሪን ድንቅ ስራና ተአምር በማድነቅና በሃያልነቱ ቸርነት ይማለደን ዘንድ ተማጽኘ ጽሁፌን ልቋጭ
ስንደፋደፍ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ደሱ ወገኛው አንድ የለጠፋት ቁም ነገር ሳበችኝ፡፡ እያደገ ያለው እስላም አክራሪነት በኢትዮጵያ
የሚል መንፈስ የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ግጭቱ ተንተርሶ በእንግሊዝኛው የሰጣት አስተያየት "Here you go!
They cook their politics and they send to us. Then we fight saying "Yes it
is True", "No it is false". . . Then they film our fight and
enjoy switching on their remote control!" የደሱን አስተያየት በድፍረት ስተርጉማት እንዲህ ትላለች
" ይህውላችሁ ! ተመልከቱ ! ፖለቲካውን እያበሰሉ ይልኩልናል
. . . እኛ "ትክክል ነው ውሽት ነው" እያልን እንፋጃለን . . . ከዚያም ፍጅታችን ይቀርጹና ተደላድለው በሚዘውሩት
የቴሌቪዥን ምስል መቀያየሪያ remote control እየቀያየሩ በደስታ ፍጅታችን ይፈረጁታል !" ያላት ቀልቤ ሳበችው !
አዎ ዜናውን አነበብኩት እንደተባለው የአሜሪካ የጸረ ሽብር አግር በሆነቸው በሃገራችን መንስግትና በሙስሊማን መካከል የተቀሰቀሰው
ግጭት ምንጩ እኔን እስከገባኝ ድረስ የኢትዮጵያን ህገ መንግስጽ አንቀጽ
ሶስት ላይ “ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ፤ ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም” በሚል የተደነገገው
ይከበር የሚል ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ እንጂ በመንግስት መገናኛ
ብዙሃንና ዛሬም በዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ሊገለጽ
 |
ሚስጥር ዘክዛኪው ዊክሊክና አሳንጅ
|
እንደተፈለገው ግጭቱ በመንግስት ወታደሮችና በሃገሪቱ እያደጉ በመጡት ሙስሊም አክራሪነት
መካከል አይደለም፡፡ ትክክለኛ መረጃ አይደለም፡፡ ይህ ዘገባ የአሜሪካው አምባሳደር ዶር ያማማቶ ወደ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ያስተላለፉትን አፈትልኮ የወጣ ሚስጥራዊን የዊክሊክ መረጃ አስታወሰኝ፡፡ እንደ መረጃው ከሆነ የቀድሞው በኢትዮጵያ የአሜሪካው አምባሳደር
ዶር ያማማቶ በግርድፉ ያሉት እስላም አክራሪነት "በውሃቢይዝም" ጀርባ በኢትዮጵያ ውስጥ የመስፋፋት አዝማሚያ ማሳየቱን
ነበር፡፡ ችግሮች አልተስተዋሉም ብየ አልከራከርም ! ያም ሆኖ አሁን በተነሳው የሙስሊማን የመብት ጥያቄ ዙሪያ የአክራሪነት መንፈስና
ጥያቄ ሃገሬን ይንጣታል ብየ አልሰጋም ፡፡ ያ መንፈስ አለ ሊያስብል የሚያስችል እውነታ የለም ባይ ነኝ ! ብቻ ሁኔታውን ረጋ ብለንና
ከስሜት ወጥተን በውል ማጤን ይገባል ስል ለዚህ ሁሉ ተንኮል ወደ ማይተኙት እጀን በመጠቆም ነው . . . የደሱን አስተያየት ልድገም
"
ፖለቲካውን እያበሰሉ ይልኩልናል . . . እኛ "ትክክል ነው ውሽት ነው" እያልን እንፋጃለን . .
. ከዚያም ፍጅታችን ይቀርጹና ተደላድለው በሚዘውሩት የቴሌቪዥን ምስል መቀያየሪያ remote control እየቀያየሩ በደስታ ፍጅታችን
ይፈረጁታል !" ለሁሉም እውነቱን ገላጭ ለሆነው ፈጣሪ እውነቱን እንዲያሳየን በመማጸንና ለድንቅ ስራው በማመስገን የማለዳ
ወጌን እቋጭ ዘንድ አሁንም የሱ ፈቃድ ሆነ !
ቸር ያሰማን
!
ነቢዩ ሲራክ