![]() |
|
የደ.ኢ.ህዴ.ን አቋም መግለጫ
ሰንድ 4ኛ ገጽ
|
አመሻሹ ላይ
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች
የጅዳ መሰረታዊ ድርጅት የጅዳ መሰረታዊ ድርጅት (ደ.ኢ.ህዴ.ን) ለእናት ማህበሩ ለኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ "በቪዛ የሚመጡ ወገኖችን
ይመለከታል" በሚል ፍሬ ሃሳብ ስር ያሰፈው አራት ገጽ ዝርዝር መግለጫና የውሳኔ ሃሳብ የተዘረዘሩ ቁም ነገሮችን ያካተተው
የደብዳቤ ኮፒ በኋላው በር ደርሶኝ በጽሞና ደግሜ ደጋግሜ ተመልክቸዋለሁ፡፡ ከሁሉም በላይ በውሳኔ ሀሳቡ ላይ የቀረበው የአቋም መግለጫ መላ ነዋሪውን በአንድ
ማዕቀፍ የሚያሰባስበውን የጅዳ ኮሚኒቲና የጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት በመጠላያ የሚገኙትን ለግፉአን ወገኖችን ለመደገፍ ለመደገፍ የጀመሩትን
እንቅስቃሴ "ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ሰምተነዋል" ይልና ኮሚኒቲው ይህን መሰል ሃላፊነት መወጣት አይችልም በማለት
ያትታል፡፡ ለዚህም የኮሚኒቲውን ብቁ አለመሆን በሚያኮስሰው አምስት የማይስማሙ ምክንያቶች አምስተኛ ተራ ላይ አነሰም በዛ በአባላት
ይሁንታ የተመረጡ የአመራር አባላት ላይ ያነጣጠረ ወቀሳውን ይሰነዝራል፡፡ እንዲህ በማለት እጠቅሳለሁ"በኮሚቲው አመራር ውስጥ
በሃገራችን የገጽታ ግንባታ ስራ ውስጥ ፖለቲካዊ ዝግጂት የሚጎላቸው አባላት አሉ፡፡" ይላል፡፡ የደቡብ ህዝቦች ንቅናቄ ኮሚኒቲው
ከዚህ መሰል እንቅስቃሴ እንዳይሳተፍ ለኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የጅዳ ጽህፈት ቤት በላከው የውሳኔ ሃሳብ ደብዳቤ ቆንስል መስሪያ ቤቱ በበላይነት
እንዲመራው በመምከር ሲያስረዳም ይህን መሰሉን ጉዳይ ለመፍታት የተቋቋመው ኮሚቴና የሴቶች ማህበርን በማጠናከር ስራው መሰራት እንዳለበት
አቋሙን በአጽንኦት ይጠይቃል፡፡
በአስገራሚው ሰነድ
የተጠቀሰው ሁሉ አነጋጋሪ ቢሆንም በገጽ ሁለት ላይ የተፈናቃዮች ቁጥር ከፍ እያለ እንደሚመጣ በማመላከት ችግሩ እየከፋ ከቁጥጥር
ውጭ እንዳይዎጣ ስጋት መኖሩን በማመላከት መፍትሄ ሃሳቡን ያመላከተበት አቅጣጫ አሳዛኝ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ሁሉንም ዜጎች በዘር
ሳይለይ ያቀፈውና በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዴራ ስር የተደራጀው ኮሚኒቲን አጣጥሎ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በመንግስት ከፍተኛ ጉትግታ
የተቋቋመውን የሴቶች ማህበርና የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ሃላፊነቱ እንዲሰጣቸው መጠየቅ ለተቸገሩት ማዘንና ለዜጎች ደህንነት ከመቆርቆር
የመነጨ አለመሆኑን ለመስገንዘብ ብዙ መሄድ ያለብኝ አይመስለኝም፡፡ የሴቶች ማህበር ለስንተኛ ጊዜ ተመስርቶ ተደራጀ ? ከዚህ በፊት
በተለያዩ ዝግጅቶች የተሰባሰበው ገንዘብ የት ገባ ? የአሁኑ ማህበርስ አባላት ስንት ናቸው ? እነማን ? ብለን ከመጠየቅ አልፈን የአሁኑ ማህበር አሁን የተሰጠውን ሃላፊነት የመወጣት
አቅም አለው ብለን ከጠየቅን ከኮሚኒቲው የተሻለ ሆኖ እንደማናገኘው በእርግጠኝነት መናገር ይችላል፡፡ ሌላው ስራውን እንዲሰራ በውሳኔ
ሃሳቡ የተጠቀሰው የመፍትሄ አፈላለጊ ኮሚቴ ሆኖ ስናገኘው ሌላውን እንቆቅልሽ እናገኘዋለን፡፡ የመፍትሄ አፈላለጊ ኮሚቴው ላለፉት
ሰባት አመታት መኖሩ እንጂ እየሰራው ስላለው ስራ ፤ ከነዋሪው በየቀኑ የሚሰበስበው ከመቶ ሽዎች ያለፈ ገንዘብ አንድም ቀን ለመረጠው
ምልአተ ጉባኤ ሪፖርት አቅርቦ የማያውቅ በጣት በሚቆጠሩ ወገኖች የሚመራ ግልጽነት የማይታይበት አካል ለመሆኑ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡
ኮሚቴው እየሰራ እያለው ግራ ያጋባቸውና ጉዳዩ ያገባናል ያሉ ወገኖች ፊርማ በማሰባሰብ እየተሰራ ስላለው ስራ ይገለጽልን ! በአዲስ
ይደራጅ አለያም መዳረሻውን እንወቀው በማለት ያቀረቡት አቤቱታ በኮሚኒቲው በኩል ለቆንስል መስሪያ ቤቱ የቀረበ ቢሆንም ላለፉት ወራት
ለዚህ የተሰጠ መልስ የለም፡፡ አሁንም በዚህ እንዘርዝር ከተባለ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ ለጊዜው ይቅር ! አዎ ከላይ በድርጅቱ የቀረበው ውሳኔ ሃሳብን አስተዛዛቢ የሚያደርገው
ይህ ግልጽነት ያልተሞላበት ድብቅ እውነት በተባሉት ማህበራት ጫንቃ ተቆልሎ ፍንትው ብሎ ሰብ አዊነት ብቻ የሚተይቀውን ስራ ኮሚኒቲው
የመሸከም አቅም የለውም ብሎ መናገር ከነባሪው እውነታ መሸሸት ነው ብሎ መደምደም አስተዛዛቢ ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡ከዚህ ተነስተን
እውነታውን ስንገመግም የኮንትራት ስለሚመጡ ዜጎችና በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ አባል ድርጅትን የሚያስረዳው ሰነድ መፍትሄ አመላካች ሊሆን
ገና ቡዙ ብዙ ይቀረዋል !
![]() |
|
ልትደፈር ስትል አመልጥ ብላ ከፎቅ ዘላ ሁለት እግሯን የተሰበረችው እህት
|
![]() |
|
ለወራት የጎስቋሎች የቆንስሉ
መጠለያ ውሎ . . .
|
ዜጎች ስራ ብለው
መጥተው ያልጠበቁት የመከራ ቀንበር ተጭኗቸው ባለበት የታሪክ አጋጣሚ አሁን በኢ.ሕ.ዴ.ግ አባል ድርጅት፤ በጥላው ስር ባሉ ድርጅቶና
በኮሚኒቲው መካከል የሚታየው ፍጥጫ መቆም ይኖርበታል፡፡"አለባብሰው
ቢያርሱ ባረም ይመለሱ" ይላሉ አባቶች ፡፡ አለባብሰን ማረሱ
የትም አያደርሰንም፡፡ ለማድረግ የተፈለገው ተፈናቃይ ወገኖችን መደገፍ ከሆነ መፍትሄው አንድና አንድ ብቻ ነው ፡፡ ተፈናቃይ ወገኖችን
በህብረት ተባብረን ከመደገፍና ከመታደግ አልፈን በተንኮም ስንነቋቆር ፤ በፖለቲካ ስንጠላለፍ እንደባጀነው በቀጣይነት በዚህ እኩይ
ምግባር መዛቀጥ የለብንም፡፡ አባቶች ያቆዩን የመተዛዘንና የመደጋገፍ ባህል ባልረባባ ተሰባሪ ፖለቲካ ከበከልነው የድረሱልኝ ጥሪ የሚያስተጋቡ ወገኖችን ጥሪ
ከመስማትና በህብረት ልንታደጋት ከምንችለው የብዙሃን ወገኖች ህይዎት ማዳን በጎ ምግባር ያራርቀናል ። የወገኖቻችን እንባ መጥረጉና ማዳኑ ታላቅ ተስፋ አንድ አምላክ ቢሆንም ከሱ በታች በቸርነቱ የተጨነቀችን ነፍስ መድረስ
የሁላችንም ግዴታ ነውና ! ይህ ቅን ተግባር የሁሉም ሃይማኖት ተከታዮች ፤ የሁሉም ቋንቋ ተናጋሪዎች ፤ የሁሉም ዜጎች ድርሻ ነው። የዜጎች መብትን ሳናስጠብቅ ዘላቂ እድገት አና ልማት ልናመጣ አንችልም። የሀገር ድንበር ተደፈረ ፤ ወገን በረሃብ
በቸነፈርና በጎርፍ አለቀ፤ ዛሬም የአባይን ድልድይ ልንሰራ ነው ፤ ብለን ቅኔ ቋጥረን ፤ አነቃቂ ጥኡመ ዜማን ደርድረን፤ በፉከራና ቀረርቶ በአንድነት የተነሳነውን ያህል ከጫፍ እስከጫፍ
መንቀሳቀሱ በፖለቲከኞቻችን "የሃገርን ገጽታ ያጎድፋል!" እንኳ ቢባል በዜጎች ላይ እየደረሰ ላለው እየከፋ ለመጣው
ነግ በኔ ነውና መላ ልንዘይድለትና በአንድነት ልንሰራ ይገባል መልዕክቴ ነው!




