Sunday, August 26, 2012

እየደረሰኝ ያለው ማስጠንቀቂያ !


     ከቀናት በፊት ለእረፍት ከከተማ ውጭ በነበርኩብት አጋጣሚ በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት በተጠራው የሃዘን ድረሱ ጥሪ አለመገኘቴ ያስቆጣቸው ወገኖች በስልክና በውስጥ መልዕክት ማስተላለፊያ በኩል ክበድ ከበድ ያሉ ስድቦችን አጉርፈውልኛል ! አመሰግናቸዋለሁ !

  የእስከ ዛሬው ተራ የወረደ ስድብ ብቻ የነበረ ቢሆንም የዛሬው Sasun Jalew Bana ከሚባል ሰው የደረሰኝ ማስጠንቀቂያ  እናጠፋሃለን!” “ካለህበት ሃገር እናባርርሃለን !” የሚል ጠንከር ያለና በነገር የተተበተበ ነው ! ዝባዝንኪውን ማስፈራሪያ ከዚህ ጎን ለጥፌዋለሁ ! ጠቅለል ሲል ግን  እንዲህ የሚል ጥቅል የውንጀላ ሃሳብን ይዟል !    የሃገርን ገጽታ የሚያጎድፍ ስራ እየሰራህ ነው ! ትዋሻለህ ! ከግንቦት 7 አባል ነህ !” ይላል ! ለኔ ይህ ውንጀላ አስገረመኝ እንጅ አላሳዘነኝም !  

   ለሰሞነኛው ማስፈራሪያ ዛቻ ምክንያት ስለሆነኝ የጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ሃዘን መግለጫ በሚመለከት የወገን የሃዘን ስሜት አነሰም በዛ በነዋሪው እየተስተናገደ ያለ ነውና በቀጣይ የማለዳ ወግ ቅኝቴ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ የምመለከተው ይሆናል፡፡ ግልጽ ለማድረግ ያህል ሀዘኑን በሚመለከት በግል እንደ አስፈላጊነቱ በሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተሰማቸው ስሜት ለማቅረብ የራሴን ዝግጂት እያደረግኩ ነው! አስገዳጅ ግን የለብኝም ! ዳሰሳየ የሚመለከተው ተቀስቅሰውውጡና እዘኑ!” የተባሉትን እይሆንም፡፡  በመሪያቸው ጥልቅ ሃዘን የተሰማቸው ወገኖችየአፍሪካ መሪ አርበኛስለሚሉበት አንድምታ በማቀርበው ዳሰሳ የምመለከተው ይሆናል ፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን  በሞታቸው አንደሰትም ! አዝነናል !” ያሉኝ ወገኖች በጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተዳደር አልተከበረም ስለሚሉት የዜጎች መብት ዙሪያም የሚያቀርቡትን መከራከሪያ መቃኘቴ አይቀርም፡፡  ይህንን ለማድረግ ነፍሴ በመፍቀዱ በግል የማቀርበው ቢሆንም  ለማንም ቢሆን ግልጽ ላደርግ የምወደው ነገር ቢኖር በማስጠንቀቂያና ማስፈራሪያ ዛቻው ከምሰራው  ግልጽ መረጃ ቅበላ የሚገታኝ የለም ! ወትሮም እንደማደርገው ከአሳፋሪው ፖለቲካ ውጭ በማተኮር በስደተኛ ዙሪያ እያደረግኩት ያለውን መረጃን የማቀበል ስራ በማስፈራሪያ በማስጠንቀቂያና ዛቻው የማላቆመው መሆኑን ግን ደጋግሜ ላረጋግጥላችሁ እዎዳለሁ ! ገዳዮች በአደባባይ የመኖራቸውን ያህል ስለ እውነት መሞትን የማይፈሩ እንዳሉ የማትረዱ ካላችሁ ተሳስታችኋል !. . . ስለ እውነት መሞት ክብር ነው !

ቸር ያሰማን ! አክባሪዎ ነቢዩ ሲራክ
Warning Massage received from
Sasun Jalew Bana  hulunim neger eyalek new ....tayaleh....we will fu24
Report · 4:34am
Sasun Jalew Bana ante werada !!!! ante bilo gondere !!!! engedilihalen tebik !!! hulem bekutitir sirachen neh yalehew gin tagisenahale !!! ahun gin ck u soon....even .we are ur friends but u ignore the great country for money....every member of ur family is  undercontrol............SOOON,,,,,,
 Yesterday August 26,2012
Report · 1:44am
Sasun Jalew Bana  we i just send u zs message as private for u coz we went to know weather you decide to live ur life OR not.....short and precised...eyeserahew yale sira ...aytekimihim asibibet bemayagebah atigiba....eskezare tagisenal ahunim edilu aleh !!!!!
Today August 26,2012
Report · 10:41am
Sasun Jalew Bana be sielent and don operate on national image
we advice u repeatedly !!!!
Report · 10:44am
Nebiyu Sirak who you are my dear ?
Report · 10:46am
Sasun Jalew Bana am an ethiopian who works to change the bad image to good image in reverse of you !!!day n night
Report · 10:47am
Sasun Jalew Bana but i wana ask u know again do u want to llive safe??
Report · 10:50am
mikerew mikerew kalhone gin mekera yimkerew ......endegonderenetih yegebah yimeslegnal.....mine eyeserah endehone wustihen adamitew
Report 10:55am
we tolled u repeatedly live ur life..leave peacefuly with ur parents......yikiribih wushetun mewashet ......lante yemitekimih yih new
Report 11:06am
hahahaha............we advic u ....afterwards we do not take the responsibility !!! thats up to u!!! thanks !!!