Monday, April 30, 2012

ከማልረሳቸው ትዝታዎች አንዱ . . . ጂዳ " ከንድራ " ከድልድዩ ስር !


 
  በቆንስሉ በር ለሳምንት ሙቀቱን ተቋቁመው የሰነበቱ ግፉአን ወደ ድልድዩ ስር ይሄዱ ዘንድ በኮሚኒቲና በልማት ማበህራት ሸምጋይ ገላጋይ ወደ ነበሩበት ጂዳ " ከንድራ " ከድልድዩ ስር ተመልሰዋል፡፡ ወደ ተለመደው ድልድይ በማቅናት መጠጊያ ካጡት መካከል አንዲት የሰባት ወር ነብሰ ጡርን ጨምሮ ከሃያ እስከ ሰላሳ ከሚጠጉት ኢትዮጵያውያን ፈዘው ግራ ገብቷቸዋል፡፡ ከኢትዮጵያውያን የሚሸሺ የአእምሮ እክል የተዳረገ ኢትዮጽያዊ ወጣትን ከሰው ፈንጠር ብሎ ተኝቷል፡፡  ሲያዩዋት የምትፍለቀለቅ ጥቁሩን አበያ ከላይዋ ላይ አውልቃ ከበሮ የምትደልቅ የአእምሮ ሁከት ያጋጠማትን እህት በድልድዩ ታዛ በፕላስቲክ ቤት ሰርታ ትዘፍናለች ትዳንሳለች ሲላት አንገቷን አቀርቅራ አይኖችዋን ከብለል ከብለል እያደረገች በቆረጣ ስታይ ልብን በሃዘን ትሰብራለች ፡፡ የልጂነት ትክለ ቁመናዋ የጠራው ፊቷና በምቀስ የቆረጠችው ጸጉርዋ በውል እንዳልተከረከመ ጎረምሳ ጸጉር እዚህ እዚያ ጉች ጉሽ ቢሉም የቀድሞ ማንነታቸውን ይመሰክራሉ፡፡ ብቻ አልፎ አልፎ ዝምታ ታበዛለች ሲላት እንዳልኩዋችሁየሚያማምሩ ከንፈሮችዋን ፍልቀቅ እያደረገች አስደንጋጭና ማራኪ ፈገግታዋን ትናኝበታለች፡፡ "ብዙ ጊዜ አይከፋትም  ! ደስተኛ ናት !  አልፎ አልፎ ደግሞ ሌላ ሰው ትሆናለች ዝም ትልና ታለቅስልች. . . እንባዋ አያቋርጥም ታንዶልድለዋልች … ይህን ያጫወተኝ እዚያ ድልድዩ ስር የከረመ ምስኪን ወንድም ነበር፡፡ ሰላም ስትሆን ችግሩ ውላ ከምታድርበት አለም ስትነቃ ፤የምታወራው የልጂነት ትዝታ ፤ የጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት የሞቀ የደመቀ የወጣትነት ህይወት፤ የደራ የሞላላቸው ቤተሰቦችዋ ፤ፍቅራቸው የሚያሳሳ ወንድሞችዋ እንክብክቤብና የሷ አዱ ገነት ሌላ ናቸው እያለ አጫወተኝ፡፡ ብቻ ይህን የምታወራው ጨለማን ተገን አድርጋ ያው ቀለል ሲላት ብቻ በመሆኑ አልተመቸኝም፡፡ ሰላም ነው ብየ የሱዋን ወግ ልዳምጥ ደጋግሜ ብሄድም አንዴ ዝም ብላ ብቻዋን እየሳቀችን እየተፍልቀልቀች ሌላ ጊዜ አኩርፋ አገኛትና ተበሳጭቸ እመለሳለሁ፡፡ . . . የዚያ ዘመን የአረብ ሃገር ህይወት ደግሞ ለአቅመ አዳም ሳይደርሱ ለአረብ ሃገር ስደት የሚዳረጉ እህቶቻችን ይትድብቀ እውነት ቁልጭ አድርጐ ያሳይል፡፡ ወደ ስራ ስሄድ ሳገድም ነቅታ አገኛታለሁ የሰማሁትን ከራሱዋ አንደበት አዳምጠዋለሁ በሚል ብዙ መድከሜ አይረሳኝም ፡፡ አንድ ቀን ግን ተሳካልኝ . . . ክቅርብ ርቀት ቁጭ ብየ እየተፍለቅለቀች ስትውጋኝ መታመሙዋን ረሳሁት፡፡ መጠየቅና መልስ ማግኘት የለም ብቻ በይ ሲላት የምትጀምረው ጨዋታዋ ምራቅ ያስውጣል፡፡ ሙሉም ባይሆን እየቦጫጨቀች ያቻወተኝ ማንነቱዋን በአንድ ጫፍ እንድረዳ ከማሳወቅ ባለፈ ከአብዮት አደባባይ እስከ ቦሌ ባለው ሰፈር የት ተወልዳ እንዳደገች ለማወቅ የሚያስችል መረጃ ማግኘት አልቻልኩም . . .

No comments:

Post a Comment