"
የሀገሬ አፈር ይብላኝ እንጅ እዚህ ምን አደርጋለሁ! "
ከወራት በፊት ይህችን
እህት ያገኘኋት ጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት መጠለያ ነበር ፡፡ ለመጣችበት የኮንትራት ቪዛ ለሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች 15 ሺህ ብር
ያላነሰ ከፍላ ራሷን ረድታ ቤተሰቦችዋን ልትደገፍ ሳውዲ ገባች፡፡ ብዙም ሳትቆይ በምትሰራበት ቤት ባለቤት ልጆች አስገድደው ሲደፍሯት
በማታውቀው ሃገር ከአሰሪዎቿ ጠፋች ! ከዚህ በኋላ ያጋጠማት የጠበቀችው አልነበረም፡፡ በተጠለልችበት መጠለያ ከጎንዋ በርከክ ብየ
ወደ ሳውዲ ያሰደዳትን የድህነት አረንቋ አስከፊ ህይወትና ከሽግሩ ለመውጣት ሳውዲ መምጣት አራጣ ተበድራ እስከመጣችበት ያለውን አሳዛኝ
የቤተሰብ ታሪኳን አጫውታኛለች፡፡ ዛሬ በአንደበቷ የምትነግራችሁ ግፍና በደል አስመርሯት ወደ ሃገሯ ለመግባት ቆርጣለች ፡፡ ያም
ሆኖ " ሰርቸ እከፍላለሁ !" ብላ ያመጣችውን የአራጣ ብድር ገንዘብ መተካት እንደማትችል ታውቀዋለች፡፡ ወደ ሃገሬ
ልመልስ ብትልም ቤተሰቦቿን ለማግኘት እንዳልሆነም ገልጻልኛለች ፡፡ ወደ ሃገርሽ የምትገቢው ቤተሰቦችሽን ለማግኘትና ህክምና እንኳ
እንድታገኝ ካልሆነ ለምን መሔዱን ፈቀድሽ ? አልኳት. . . እዳ ያወረሰቻቸውን ቤተሰቦች ፈጽሞ እንደማትቀላቀል ገልጻልኝ " ያገሬ አፈር ይብላኝ እንጅ እዚህ ምን
አደርጋለሁ!" ነበር ያለችኝ እንባዋን እያዘራች. . . ! ከብዙ እንግልት በኋላ ይህች እህት ከወራት በፊት ለበደሏ ፍትህን
ሳታገኝ ወደ ሃገር ቤት መግባቷን ሰምቻለሁ ! ይህስ በኮንትራት ሰራተኞች
ዙሪያ እየሆነ ያለውን የተደበቀ እውነት ያሳይልኝ ይሆን ?
No comments:
Post a Comment